Tuesday, March 20, 2012

ስፖንሰር ያገኙ ሕጻናት ዝርዝር

ወዳጆች እንዴት ናችሁ?

ሌሎችን መርዳት እንዳለብን ስናስብ ብዙ ጊዜ፣ የራሳችን ጉድለቶች ወደ አይምሮአችን መምጣታቸው አይቀርም። ‘’ስንት ጉድለት እያለብኝ፣ እንዴት ነው ሌላውን ላስብ የምችለው?’’ እንል ይሆናል። እንደ እኔ እምነት ጥያቄው በራሱ ስህተት የለውም። ሆኖም ጥያቅው በውስጡ የሸሸገው ስስት እና ራስ ወዳድነት ሊኖረው እንደሚችል ግን እጠራጠራለው። መቼም ቢሆን ፍላጎቶቻችን አይሞሉም። አንዱ ሲሞላ ሌላ በር ይከፈታል፣ እሱም ሲሞላ ሌላ ይመጣል። በሰው ፍላጎት ውስጥ በቃኝ የሚል ምኞት ያልተፈጠረ እስኪመስል ድረስ፣ አንዱን ስናገኝ ሌላውን ለመሙላት መባዘናችን የተለመደ የቀን ተቀን ተግባራችን ነው ብል ያጋነንኩ አይመስለኝም።

ሁለት ያለው አንዱን ይስጥ የሚለው የጌታችን እና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ፣ የሚመለከተን እስካይመስል ድረስ ኑሮችን ሁሉ በማግበስበስ እና በማከማቸት ላይ ያተኮረ ነው የሚለው ሃሳብ በዚህ 21ኛው ክፍለ ዘመን የምንኖር ክርስቲያኖችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከት ይመስለኛል።

ራሳችንን እና ዘመድ አዝማዶቻችንን ወይም ቤተሰቦቻችንን ብቻ ከማየት አዙሪት ወጥተን ብድራችንን የማይከፍሉትን፣ መልሰው ሊያመሰግኑን የማይችሉትን ሌሎች ችግረኞችን ለመርዳት በመነሳት ሙሉ ክብር ለእግዚአብሔር እናምጣ።

በዚህ ገጽ ውስጥ ስማቸውን እና ፎቶአቸውን የምትመለከቱት ሕጻናት ለዚህ ጥሪ ፊታቸውን ባላዞሩ ሰዎች ስፖንሰር የተደረጉ ናቸው። እርሶም የዚህ ጥሪ ተካፋይ ሊሆኑ ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃ የሚሹ ከሆነ በሚከተለው የኢ-ሜይል አድራሻ ያግኙን kidsfirstethiopia@gmail.com ልጆቹ ስለሚያገኙት ጥቅም እና ስለ ፕሮጀክቱ ዝርዝር መረጃ ማግኘት የሚሹ ከሆነ ደግሞ ሊንኩን ይጫኑ። ይህን ፕሮጀክት ለመቀላቀል እየፈለጉ ነገር ግን ገንዘብ አጠቃቀሙን በተመለከተ የእምነት ጥያቄ ካለብዎ፣ አንድ ምክር እንለግስዎ። እንዲህ አይነቱን ፕሮጀክት ራስዎ በዙሪያዎ ካሉ ጥቂት ሰዎች ጋር በጋራ በመሆን ለምን አይጀምሩም? ይህንን ፕሮጀክት ኮፒ እንዲያደርጉ ሙሉ ፈቃደኞች ከመሆናችን በተጨማሪ የሃሳብ እገዛም ለማድረግ ከጎንዎ እንቆማለን። 

ስማቸው ከዚህ በታች ተዘረዘሩት ሰዎች እስከ አሁን  ሕጻናቱን ስፖንሰር ለማድረግ በፕሮጀክቱ የታቀፉ ናቸው።     
 1. አዳነው ዲሮ
 2. ናኦሚ ጌታነህ
 3. ሱራፌል እና መአዛ ሃይሌ
 4. ፊኒ
 5. ፍሬ
 6. ዳንኤል ነጋሽ
 7. ሐይሚ ይደንግጡ
 8. ሀሪ መንገሻ (2ልጆች)
 9. ሀሪ መንገሻ
 10. አሚ ጎርፉ
 11. ዮናስ
 12. አብርሃም  ሀይሌ እና ሃና ሀይሌ