Tuesday, April 10, 2012

አፎሚያ ኤርምያስ


አፎሚያ ኤርምያስ

ምህረት ዳንኤል


ምህረት ዳንኤል ፍስሀ

ቴዎድሮስ አለማየው


ቴዎድሮስ አለማየው

ትዝታ በርክት


ትዝታ በርክት

አልዓዛር ሳሙኤል


አልዓዛር ሳሙኤል

አቤል ምትኩ


አቤል ምትኩ

ዕዝራ ግርማ


ዕዝራ ግርማ

ዬሴፍ በርክት


ዬሴፍ በርክት

ዮናስ ሳሙኤል


ዮናስ ሳሙኤል

ትዝታ በረከት እና ዮሴፍ በረከት

ከድሆች ሕይወት ጋር የተያያዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ዘጸ. 22፡25 ከአንተ ጋር ለተቀመጠው ለወገኔ ለድሀው ገንዘብ ብታበድረው፥ እንደ ባለ አራጣ አትሁን፥ አራጣም አትጫንበት።
ዘጸ. 23፡3 በፍርድ ነገርም ለድሀው አታድላ።
ዘጸ. 23፡6 በሚምዋገትበት ጊዜ የድሀህን ፍርድ አታጥምም።
ዘጸ. 23፡10-11 ስድስት ዓመት ምድርህን ዝራ፥ ፍሬዋንም አግባ። በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት አሳርፋትም የሕዝብህም ድሆች ይበሉታል ያስቀሩትንም የሜዳ እንስሳ ይብላው። እንዲሁም በወይንህና በወይራህ አድርግ።
ዘጸ. 30፡15 ለነፍሳችሁ ማስተስረያ የእግዚአብሔርን ስጦታ ስትሰጡ ባለ ጠጋው ከሰቅል ግማሽ አይጨምር፥ ድሀውም አያጕድል።
ዘሌ. 19፡10 የወይንህንም ቃርሚያ አትቃርም፥ የወደቀውንም የወይንህን ፍሬ አትሰብስብ ለድሆችና ለእንግዶች ተወው እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
ዘሌ. 19፡15 በፍርድ ዓመፃ አታድርጉ ለድሀ አታድላ፥ ባለ ጠጋውንም አታክብር ነገር ግን ለባልንጀራህ በእውነት ፍረድ።
ዘሌ. 23፡22 የምድራችሁንም መከር በሰበሰባችሁ ጊዜ የእርሻችሁን ድንበር ፈጽማችሁ አትጨዱ፥ የመከሩንም ቃርሚያ አትልቀሙ ለድሆችና ለእንግዶች ተዉት እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
ዘሌ. 25፡25 ወንድምህም ቢደኸይ ከርስቱም ቢሸጥ፥ ለእርሱ የቀረበ ዘመዱ መጥቶ ወንድሙ የሸጠውን ይቤዠዋል።
ዘሌ. 25፡ 35 ወንድምህ ቢደኸይ እጁም በአንተ ዘንድ ቢደክም፥ አጽናው እንደ እንግዳና እንደ መጻተኛም ከአንተ ጋር ይኑር።
ዘሌ. 25፡39 ወንድምህም ቢደኸይ ራሱንም ለአንተ ቢሸጥ፥ እንደ ባሪያ አድርገህ አትግዛው።
ዘሌ. 25፡47-48 በአንተም ዘንድ የሚኖር መጻተኛ ወይም እንግዳ ሀብታም ቢሆን፥ ወንድምህም በእርሱ አጠገብ ቢደኸይ፥ ራሱንም ለመጻተኛው ወይም ለእንግዳው ወይም ለወገኖቹ ዘር ቢሸጥ፥ ከተሸጠ በኋላ መቤዠት ይችላል ከወንድሞቹ አንዱ ይቤዠው…
ዘዳ. 15፡4-5 አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ ርስት አድርጎ በሰጠህ ምድር ላይ እግዚአብሔር በእውነት ይባርክሃልና አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ፈጽመህ ብትሰማ፥ ታደርጋትም ዘንድ ዛሬ የማዝዝህን ይህችን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቅ፥ በመካከልህ ድሀ አይኖርም።
ዘዳ. 15፡7 ምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ በአገርህ ደጅ ውስጥ ከሚኖሩ ከወንድሞችህ አንዱ ቢደኸይ፥ ልብህን አታጽና፥ በድሀው ወንድምህ ላይ እጅህን አትጨብጥ።
ዘዳ. 15፡9 ሰባተኛው ዓመት የዕዳ ምሕረት ዓመት ቀርቦአል ብለህ ክፉ አሳብ በልብህ እንዳታስብ፥ ለድሀውም ወንድምህ አንዳች የማትሰጥ እንዳትሆን፥ ዓይንህም በእርሱ ላይ ክፉ እንዳይሆን፥ እርሱም ወደ እግዚአብሔር በአንተ ላይ እንዳይጮህ፥ ኃጢአትም እንዳይሆንብህ ተጠንቀቅ።
ዘዳ. 15፡11 ድሆች ከምድሪቱ ላይ አያልቁምና ስለዚህ እኔ። በአገርህ ውስጥ ላለው ድሀ ለተቸገረውም ወንድምህ እጅህን ትከፍታለህ ብዬ አዝዝሃለሁ።
ዘዳ. 24፡10-15 ለባልንጀራህ ባበደርኸው ጊዜ መያዣውን ልትወስድ ወደ ቤቱ አትግባ። አንተ በውጭ ቁም ያበደርኸውም ሰው መያዣውን ያውጣልህ። ያም ሰው ድሃ ቢሆን መያዣውን በአንተ ዘንድ አታሳድር። ለብሶት እንዲተኛ እንዲባርክህም ፀሐይ ሳይገባ መያዣውን ፈጽመህ መልስለት በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት ጽድቅ ይሆንልሃል ድሀና ችግረኛ የሆነውን ምንደኛ፥ ከወንድሞችህ ወይም በምድርህ በአገርህ ደጅ ውስጥ ከሚቀመጡት መጻተኞች ቢሆን፥ አታስጨንቀው። ድሀ ነውና፥ ነፍሱም ጠንክራ ትፈልገዋለችና ወደ እግዚአብሔር እንዳይጮኽብህ ኃጢአትም እንዳይሆንብህ ደመወዙን ፀሐይ ሳይገባ በቀኑ ስጠው።
1ሳሙ. 2፡7-8 እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል። ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ።
አስቴር 9፡21-22 በየዓመቱም አዳር በሚባለው ወር አሥራ አራተኛውና አሥራ አምስተኛው ቀን፥ አይሁድ ከጠላቶቻቸው ዕረፍትን ያገኙበት ቀን፥ ወሩም ከኀዘን ወደ ደስታ ከልቅሶም ወደ መልካም ቀን የተለወጠበት ወር ሆኖ ይጠብቁት ዘንድ፥ የግብዣና የደስታም ቀን፥ እርስ በርሳቸውም ስጦታ የሚሰጣጡበትና ለድሆች ስጦታ የሚሰጡበት ቀን ያደርጉት ዘንድ አዘዛቸው።
ኢዮብ 5፡15-16 ድሀውንም ከአፋቸው ሰይፍ ከኃያሉም እጅ ያድነዋል። ለምስኪኑም ተስፋ አለው ክፋት ግን አፍዋን ትዘጋለች።
ኢዮብ 20፡17-21 የማሩንና የቅቤውን ፈሳሽ ወንዞቹንም አይመለከትም። የድካሙን ፍሬ ሳይውጠው ይመልሰዋል እንደ ንግዱም ትርፍ አይደሰትም። ድሀውን አስጨንቆአል፥ ትቶታልም ያልሠራውንም ቤት በዝብዞአል። ሆዱ ዕረፍትን አላወቀምና የወደደው ነገር አላዳነውም። እርሱ ከበላ በኋላ ምንም አልተረፈም ስለዚህ በረከቱ አይከናወንለትም።
ኢዮብ 24፡3-4 የድሀ አድጎቹን አህያ ይነዳሉ የመበለቲቱን በሬ ስለ መያዣ ይወስዳሉ። ድሆቹን ከመንገዱ ያወጣሉ የምድርም ችግረኞች ሁሉ ይሸሸጋሉ።
ኢዮብ 24፡9 ድሀ አደጉን ልጅ ከጡቱ የሚነጥሉ አሉ ከችግረኛውም መያዣ ይወስዳሉ።
ኢዮብ 24፡14 ነፍሰ ገዳዩም ሳይነጋ ማልዶ ይነሣል ችግረኞችንና ድሆችን ይገድላል፤ በሌሊትም እንደ ሌባ ነው።
ኢዮብ 29፡12 የሚጮኸውን ችግረኛ፥ ድሀ አደጉንና ረጂ የሌለውን አድኜ ነበርሁና።
ኢዮብ 29፡16 ለድሀው አባት ነበርሁ የማላውቀውንም ሰው ሙግት መረመርሁ።
ኢዮብ 30፡25 ጭንቅ ቀን ላገኘው ሰው አላለቀስሁምን? ለችግረኛስ ነፍሴ አላዘነችምን
ኢዮብ 31፡16-19 ድሀውን ከልመናው ከልክዬ፥ የመበለቲቱን ዓይን አጨልሜ እንደ ሆነ፥ እንጀራዬን ለብቻዬ በልቼ እንደ ሆነ፥ ድሀ አደጉም ደግሞ ከእርሱ ሳይበላ ቀርቶ እንደ ሆነ፤ እርሱን ግን ከታናሽነቴ ጀምሬ እንደ አባቱ ከእኔ ጋር አሳድጌው ነበር፥ እርስዋንም ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ መራኋት፤ ራቁቱን የሆነው ሰው ሲጠፋ፥ ወይም ድሀ ያለ ልብስ ሲሆን አይቼ እንደ ሆነ፥
ኢዮብ 34፡19 እነርሱ ሁሉ የእጁ ሥራ ናቸውና በአለቆች ፊት አያደላም፥ ባለጠጋውንም ሰው ከድሀው ይበልጥ አይመለከትም።
ኢዮብ 34፡27-28 የድሀውን ልቅሶ ወደ እርሱ ያደርሱ ዘንድ፥ እርሱም የችግረኛውን ድምፅ ይሰማ ዘንድ፥ እርሱን ከመከተል ፈቀቅ ብለዋልና፥ ከመንገዱም ሁሉ አንዱን አልተመለከቱምና።
ኢዮብ 36፡6 እርሱ የበደለኞችን ሕይወት አያድንም ለችግረኞች ግን ፍርዱን ይሰጣል።
ኢዮብ 36፡15 የተቸገረውን በችግሩ ያድነዋል በመከራም ጆሮአቸውን ይገልጣል።
መዝ. 9፡18 ድሀ ለዘላለም አይረሳምና፥ የችግረኞችም ተስፋቸው ለዘላለም አይጠፋም።
መዝ. 10፡2 በኃጢአተኛ ትዕቢት ድሀ ይናደዳል ባሰቡት ተንኰላቸው ተጠመዱ።
መዝ. 10፡8-14 በመንደሮች መሸመቅያ ይቀመጣል ንጹሓንን በስውር ይገድል ዘንድ ዓይኖቹም ወደ ድኃ ይመለከታሉ።
እንደ አንበሳ በችፍግ ዱር በስውር ይሸምቃል ድሀውን ለመንጠቅ ያደባል ድሀውን ይነጥቀዋል በአሽክላውም ይስበዋል።
ድሀ ይዋረዳል፥ ይጐብጣል በኃያላኑም እጅግ ይወድቃል። በልቡም ይላል። እግዚአብሔር ረስቶኛል ፈጽሞም እንዳያይ ፊቱን ሰወረ።
አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ተነሥ እጅህም ከፍ ከፍ ትበል ድሆችን አትርሳ። ኃጢአተኛ ስለ ምን እግዚአብሔርን አስቈጣው? በልቡ። አይመራመረኝም ይላልና። አየኸው፥ አንተ ክፋትንና ቍጣን ትመለከታለህና በእጅህ ፍዳውን ለመስጠት ድሀ ራሱን ለአንተ ይተዋል፥ ለድሀ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ።
መዝ. 12፡5 ስለ ድሆች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት እግዚአብሔር፦ አሁን እነሣለሁ ይላል መድኃኒትን አደርጋለሁ፥ በላዩም እገልጣለሁ።
መዝ. 14፡6 (አ.መ.ት.) እናንተ የድሆችን እቅድ ለማፋለስ ትሻላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን መጠጊያቸው ነው።
መዝ. 34፡6 ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው፥ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።
መዝ. 35፡10 አጥንቶቼ ሁሉ እንዲህ ይሉሃል። አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? ችግረኛን ከሚቀማው እጅ፥ ችግረኛንና ድሀውንም ከሚነጥቀው እጅ ታድነዋለህ።
መዝ. 37፡ 14-15 ኃጢአተኞች ሰይፋቸውን መዘዙ፥ ቀስታቸውንም ገተሩ ድሀውንና ችግረኛውን ይጥሉ ዘንድ ልበ ቅኖችንም ይወጉ ዘንድ ሰይፋቸው ወደ ልባቸው ይግባ፥ ቀስታቸውም ይሰበር።
መዝ. 40፡17 እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፥ ጌታ ግን ያስብልኛል አንተ ረዳቴና መድኃኒቴ ነህ አምላኬ ሆይ፥ አትዘግይ።
መዝ. 41፡1-2 ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል። እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፥ ሕያውም ያደርገዋል፥ በምድር ላይም ያስመሰግነዋል፥ በጠላቶቹም እጅ አያሳልፈውም።
መዝ. 68፡10 እንስሶችህ በውስጡ አደሩ አቤቱ፥ በቸርነትህ ለድሆች አዘጋጀህ።
መዝ. 69፡29 እኔ ችግረኛና ቍስለኛ ነኝ አቤቱ፥ የፊትህ መድኃኒት ይቀበለኝ።
መዝ. 69፡32-33 ችግረኞች ያያሉ ደስ ይላቸዋል እግዚአብሔርን ፈልጉ ሕያዋንም ሁኑ። እግዚአብሔር ችግረኞችን ሰምቶአልና፥ እስረኞቹንም አልናቀምና።
መዝ. 70፡5 እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ አቤቱ፥ እርዳኝ ረዳቴ ታዳጊዬም አንተ ነህ አቤቱ፥ አትዘግይ።
መዝ. 72፡1-4 አቤቱ፥ ፍርድህን ለንጉሥ ስጥ፥ ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ፥ ሕዝብህን በጽድቅ፥ ችግረኞችህንም በፍርድ ይዳኝ ዘንድ።
ተራሮችና ኰረብቶች ለሕዝብህ ሰላምን ይቀበሉ። ለችግረኞች ሕዝብ በጽድቅ ትፈርዳለህ የድሆችንም ልጆች ታድናለህ ክፉውንም ታዋርደዋለህ።
መዝ. 72፡12-13 ችግረኛውን ከቀማኛው እጅ፥ ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና። ለችግረኛና ለምስኪን ይራራል፥ የችግረኞችንም ነፍስ ያድናል።
መዝ. 74፡19-21 የምትገዛልህን ነፍስ ለአራዊት አትስጣት የችግረኞችህን ነፍስ ለዘወትር አትርሳ። ወደ ኪዳንህ ተመልከት፥ የምድር የጨለማ ስፍራዎች በኅጥኣን ቤቶች ተሞልተዋልና። ችግረኛ አፍሮ አይመለስ ችግረኛና ምስኪን ስምህን ያመሰግናሉ።
መዝ. 82፡3-4 ለድሆችና ለድሀ አደጎች ፍረዱ ለችግረኛውና ለምስኪኑ ጽድቅ አድርጉ ብቸኛውንና ችግረኛውን አድኑ ከኃጢአተኞችም እጅ አስጥሉአቸው።
መዝ. 86፡1 አቤቱ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድምጠኝም፥ ችግረኛና ምስኪን ነኝና።
መዝ. 107፡41 ችግረኛንም ከችግሩ ረዳው እንደ በጎች መንጋ ወገን አደረገው።
መዝ. 109፡16 ምሕረትን ያደርግ ዘንድ አላሰበምና ችግረኛንና ምስኪንን ልቡ የተሰበረውንም ሰው ይገድል ዘንድ አሳደደ።
መዝ. 109፡31 ነፍሱን ከሚያሳድዱአት ያድን ዘንድ በድሀ ቀኝ ቆሞአልና።
መዝ. 112፡9 በተነ ለችግረኞችም ሰጠ ጽድቁ ለዘላለም ዓለም ይኖራል ቀንዱ በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
መዝ. 113:7-8 ከአለቆች ጋር ከሕዝቡም አለቆች ጋር ያኖረው ዘንድ ችግረኛን ከመሬት የሚያነሣ፥ ምስኪኑንም ከፋንድያ ከፍ ከፍ የሚያደርግ
መዝ. 132:15 አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ።
መዝ. 140:12 እግዚአብሔር ለድሀ ዳኝነትን ለችግረኛም ፍርድን እንዲያደርግ አወቅሁ።
ምሳሌ 10፡4 የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች የትጉ እጅ ግን ባለጠጋ ታደርጋለች።
ምሳሌ 10፡15 የባለጠጋ ሀብት ለእርሱ የጸናች ከተማ ናት የድሆች ጥፋት ድህነታቸው ነው።
ምሳሌ 13፡7-8 ራሱን ባለጠጋ የሚያስመስል ሰው አለ፥ ነገር ግን አንዳች የለውም ራሱን ድሀ የሚያስመስል አለ፥ ነገር ግን እጅግ ባለጠግነት አለው። ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም።
ምሳሌ 13፡23 በድሆች እርሻ ላይ ብዙ ሲሳይ አለ ከፍርድ መጕደል የተነሣ ግን ይጠፋል።
ምሳሌ 14፡20-21 ድሀ በባልንጀራው ዘንድ የተጠላ ነው የባለጠጋ ወዳጆች ግን ብዙዎች ናቸው። ባልንጀራውን የሚንቅ ይበድላል ለድሀ ግን የሚራራ ምስጉ ነው።
ምሳሌ 14፡31 ድሀን የሚያስጨንቅ ፈጣሪውን ይሰድባል ለድሀ ምሕረትን የሚያደርግ ግን ያከብረዋል።
ምሳሌ 17፡5 በድሀ የሚያላግጥ ፈጣሪውን ይሰድባል በጥፋትም ደስ የሚለው ሳይቀጣ አይቀርም።
ምሳሌ 18፡23 ድሀ በትሕትና እየለመነ ይናገራል ባለጠጋ ግን በድፍረት ይመልሳል።
ምሳሌ 19፡1 በከንፈሩ ከሚወሳልት ሰነፍ ይልቅ ያለ ነውር የሚሄድ ድሀ ይሻላል።
ምሳሌ 19፡4 ባለጠግነት ብዙ ወዳጆች ይጨምራል የድሀ ወዳጅ ግን ከእርሱ ይርቃል።
ምሳሌ 19፡7 ድሀን ሰው ወንድሞቹ ሁሉ ይጠሉታል ይልቁንም ወዳጆቹ ከእርሱ ይርቃሉ። እነርሱንም በቃል ቢከተላቸው አንዳች አይረቡትም።
ምሳሌ 19፡17 ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።
ምሳሌ 19፡22 የሰው ቸርነት የእርሱ ፍሬ ነው ከሐሰተኛ ባለጠጋም እውነተኛ ድሀ ይሻላል።
ምሳሌ 21፡13 የድሀውን ጩኸት እንዳይሰማ ጆሮውን የሚደፍን ሰው፥ እርሱ ራሱ ይጮኻል አይሰማለትምም።
ምሳሌ 21፡17 ተድላ የሚወድድ ድሀ ይሆናል፥ የወይን ጠጅንና ዘይትንም የሚወድድ ባለጠጋ አይሆንም።
ምሳሌ 22፡2 (አ.መ.ት.) ባለጠጋና ድሃ የሚጋሩት ነገር፣ እግዚአብሔር የሁለታቸውም ፈጣሪ መሆኑ ነው።
ምሳሌ 22፡7 ባለጠጋ ድሆችን ይገዛል፥ ተበዳሪም የአበዳሪ ባሪያ ነው።
ምሳሌ 22፡9 ርኅሩህ የተባረከ ይሆናል፥ ከእንጀራው ለድሀ ሰጥቶአልና።
ምሳሌ 22፡16 ለራሱ ጥቅም ለመጨመር ሲል ድሀን የሚጐዳ፥ ለባለጠጋም የሚሰጥ፥ እርሱ ወደ ድህነት ይወድቃል።
ምሳሌ 22፡22 (አ.መ.ት.) ድሆች በመሆናቸው ብቻ ድሆችን አትበዝብዛቸው፤ ችግረኛውንም በአደባባይ አታንገላታው።
ምሳሌ 28፡3 ድሆችን የሚያስጨንቅ ምስኪን ሰው እህልን እንደሚያጠፋ እንደ ዶፍ ዝናብ ነው።
ምሳሌ 28፡6 በጠማማ መንገድ ከሚሄድ ባለጠጋ ያለ ነውር የሚሄድ ድሀ ይሻላል።
ምሳሌ 28፡8 በአራጣ ብዛትና በቅሚያ ሀብቱን የሚያበዛ ለድሀ ለሚራራ ያከማችለታል።
ምሳሌ 28፡11 (አ.መ.ት.) ባለጠጋ ራሱን ጠቢብ አድርጎ ይቆጥር ይሆናል፤ አስተዋይ የሆነ ድሃ ግን መርምር ያውቀዋል።
ምሳሌ 28፡15 በድሀ ሕዝብ ላይ የሚገዛ ክፉ መኰንን እንደሚያገሣ አንበሳን እንደ ተራበ ድብ ነው።
ምሳሌ 28፡27 ለድሀ የሚሰጥ አያጣም ዓይኖቹን የሚጨፍን ግን እጅግ ይረገማል።
ምሳሌ 29፡7 ጻድቅ የድሆችን ፍርድ ይመለከታል ኀጥእ ግን እውቀትን አያስተውልም።
ምሳሌ 29፡14 ለድሀ በእውነት የሚፈርድ ንጉሥ፥ ዙፋኑ ለዘላለም ይጸናል።
ምሳሌ 30፡7-9 ሁለትን ነገር ከአንተ እሻለሁ፥ ሳልሞትም አትከልክለኝ ከንቱነትንና ሐሰተኛነትን ከእኔ አርቃቸው ድኅነትንና ባለጠግነትን አትስጠኝ ነገር ግን የሚያስፈልገኝን እንጀራ ስጠኝ፥ እንዳልጠግብ እንዳልክድህም። እግዚአብሔርስ ማን ነው? እንዳልል ድሀም እንዳልሆን እንዳልሰርቅም፥ በአምላኬም ስም በሐሰት እንዳልምል።
ምሳሌ 30፡14 ድሆችን ከምድር ላይ ችግረኞችንም ከሰው መካከል ያጠፋና ይጨርስ ዘንድ ጥርሶቹ ሰይፍ መንጋጎቹም ካራ የሆኑ ትውልድ አለ።
ምሳሌ 31፡9 አፍህን ክፍት፥ በእውነትም ፍረድ ለድሀና ለምስኪን ፍረድ።
ምሳሌ 31፡ 10-20 ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? … እጅዋን ወደ ድሀ ትዘረጋለች፥ ወደ ችግረኛም እጅዋን ትሰድዳለች።
መክ. 4፡13-14 ድሀና ጠቢብ ብላቴና ተግሣጽን መቀበል ከእንግዲህ ወዲህ ከማያውቅ ከሰነፍ ሽማግሌ ንጉሥ ይሻላል።
ምንም በመንግሥቱ አገር ደግሞ ችግረኛ ሆኖ ቢወለድ፥ ከግዞቱ ቤት ወደ መንግሥት ወጥቶአልና።
መክ. 5፡8 ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ይመለከታልና፥ ከእነርሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላሉና በአገሩ ድሆች ሲገፉ፥ ፍርድና ጽድቅም ሲነጠቅ ባየህ ጊዜ በዚህ ነገር አታድንቅ።
መክ. 9፡15-16 ጠቢብ ድሀ ሰውም ተገኘባት፥ ያችንም ከተማ በጥበቡ አዳናት ያን ድሀ ሰው ግን ማንም አላሰበውም።
እኔም። ከኃይል ይልቅ ጥበብ ትበልጣለች የድሀው ጥበብ ግን ተናቀች ቃሉም አልተሰማችም አልሁ።
ኢሳ. 3፡14-15 እግዚአብሔር ከሕዝቡ ሽማግሌዎችና ከአለቆቻቸው ጋር ይፋረዳል የወይኑን ቦታ የጨረሳችሁ እናንተ ናችሁ ከድሆች የበዘበዛችሁት በቤታችሁ አለ ሕዝቤንም ለምን ታደቅቁአቸዋላችሁ? የድሆችንስ ፊት ለምን ትፈጫላችሁ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦
ኢሳ. 10፡1-2 መበለቶችም ቅሚያቸው እንዲሆኑ፥ ድሀ አደጎችንም ብዝበዛቸው እንዲያደርጉ፥ የድሀውን ፍርድ ያጣምሙ ዘንድ፥ የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ ያጐድሉ ዘንድ የግፍን ትእዛዛት ለሚያዝዙ፥ ክፉንም ጽሕፈት ለሚጽፉ ወዮላቸው!
ኢሳ. 11፡1-4 ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል … ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፥ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል በአፉም በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
ኢሳ. 25፡1-4 አቤቱ፥ አንተ አምላኬ ነህ … የጨካኞችም ቍጣ እስትንፋስ ቅጥርን እንደሚመታ ዐውሎ ነፋስ በሆነ ጊዜ፥ ለድሀው መጠጊያ፥ ለችግረኛው በጭንቁ ጊዜ መጠጊያ፥ ከውሽንፍር መሸሸጊያ ከሙቀትም ጥላ ሆነሃል።
ኢሳ. 29፡19 የዋሃን ደስታቸውን በእግዚአብሔር ያበዛሉ፥ በሰዎች መካከል ያሉ ችግረኞችም ሐሤትን በእስራኤል ቅዱስ ያደርጋሉ።
ኢሳ. 32፡7 ንፉግም ዕቃ ክፉ ናት ችግረኛ ቅን ነገርን በተናገረ ጊዜ እንኳ እርሱ በሐሰት ቃል ድሀውን ያጠፋ ዘንድ ክፉን አሳብ ያስባል።
ኢሳ. 41፡17 ድሆችና ምስኪኖችም ውኃ ይሻሉ አያገኙምም፥ ምላሳቸውም በጥማት ደርቋል እኔ እግዚአብሔር እሰማቸዋለሁ፥ የእስራኤል አምላክ እኔ አልተዋቸውም።
ኢሳ. 58፡6-7 እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን? እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
ኤር. 2፡1-34 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። ሂድ፥ በኢየሩሳሌም ጆሮ ጩኽ፥ እንዲህም በል። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ … በእጆችሽም የንጹሐን ድሆች ደም ተገኝቶአል በእነዚህ ሁሉ ላይ በግልጥ አገኘሁት እንጂ በስውር ፈልጌ አላገኘሁትም።
ኤር. 5፡4 የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና እነዚህ በእውነት ድሆችና ሰነፎች ናቸው …
ኤር. 20፡13 ለእግዚአብሔር ዘምሩ እግዚአብሔርንም አመስግኑ የችግረኛውን ነፍስ ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና።
ኤር. 22፡1-16 ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት ውረድ በዚያም ይህን ቃል ተናገር፥ … የድሀውንና የችግረኛውን ፍርድ ይፈርድ ነበር፥ በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖ ነበር። ይህ እኔን ማወቅ አይደለምን? ይላል እግዚአብሔር፦
ሕዝ. 16፡49 እነሆ፥ የእኅትሽ የሰዶም ኃጢአት ይህ ነበረ ትዕቢት እንጀራን መጥገብ መዝለልና ሥራ መፍታት በእርስዋና በሴቶች ልጆችዋ ነበረ፥ የችግረኛውንና የድሀውንም እጅ አላጸናችም።
ሕዝ. 18፡12-13 ድሀውንና ችግረኛውንም ቢያስጨንቅ ቢቀማም መያዣውንም ባይመልስ ዓይኖቹንም ወደ ጣዖታት ቢያነሣ ርኩስን ነገር ቢያደርግ፥ በአራጣ ቢያበድር፥ ትርፎቻም ቢወስድ፥ በውኑ እርሱ በሕይወት ይኖራልን? በሕይወት አይኖርም ይህን ርኵሰት ሁሉ አድርጎአልና ፈጽሞ ይሞታል ደሙ በላዩ ላይ ይሆናል።
ሕዝ. 22፡29-31 የምድርን ሕዝብ ግፍ አደረጉ ቅሚያም ሠሩ ድሆችንና ችግረኞችን አስጨነቁ፥ መጻተኛውንም በደሉ።
ቅጥርን የሚጠግንን፥ ምድሪቱንም እንዳላጠፋት በፈረሰበት በኩል በፊቴ የሚቆምላትን ሰው በመካከላቸው ፈለግሁ፥ ነገር ግን አላገኘሁም። ስለዚህ ቍጣዬን አፈሰስሁባቸው፥ በመዓቴም እሳት አጠፋኋቸው መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ መለስሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
ዳን. 4፡27 ንጉሥ ሆይ፥ ስለዚህ ምናልባት የደኅንነትህ ዘመን ይረዝም እንደ ሆነ ምክሬ ደስ ያሰኝህ ኃጢአትህንም በጽድቅ፥ በደልህንም ለድሆች በመመጽወት አስቀር።
አሞጽ 2፡6-7 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጻድቁን ስለ ብር፥ ችጋረኛውንም ስለ አንድ ጥንድ ጫማ ሽጠውታልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የእስራኤል ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም። የድሆችን ራስ በምድር ትቢያ ላይ ይረግጣሉ፥ የትሑታንንም መንገድ ያጣምማሉ ቅዱሱንም ስሜን ያረክሱ ዘንድ አባትና ልጁ ወደ አንዲት ሴት ይገባሉ
አሞጽ 4፡1-2 በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ፥ ድሆችንም የምትበድሉ፥ ችጋረኞችንም የምታሰጨንቁ፥ ጌቶቻቸውንም። አምጡ እንጠጣ የምትሉ እናንተ የባሳን ላሞች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ። ጌታ እግዚአብሔር፦ እናንተን በሰልፍ ዕቃ፥ ቅሬታችሁንም በመቃጥን የሚወስዱበት ቀን፥ እነሆ፥ በላያችሁ ይመጣል ብሎ በቅዱስነቱ ምሎአል።
አሞጽ 5፡11-12 ድሀውንም ደብድባችኋልና፥ የስንዴውንም ቀረጥ ከእርሱ ወስዳችኋልና ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ሠርታችኋል፥ ነገር ግን አትቀመጡባቸውም ያማሩ የወይን ቦታዎች ተክላችኋል፥ ነገር ግን ከወይን ጠጃቸው አትጠጡም። ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችጋረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ፥ በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና።
አሞጽ 8፡4-6 ችጋረኛውን የምትውጡ፥ የአገሩንም ድሀ የምታጠፉ እናንተ ሆይ። እህልን እንሸጥ ዘንድ መባቻው መቼ ያልፋል? የኢፍ መስፈሪያውንም እያሳነስን፥ ሰቅሉንም እያበዛን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እያታለልን፥ ድሀውን በብር ችጋረኛውንም በአንድ ጥንድ ጫማ እንገዛ ዘንድ፥ የስንዴውን ግርድ እንሸጥ ዘንድ ስንዴውን እንድንሸምት ሰንበት መቼ ያልፋል? የምትሉ እናንተ ሆይ፥ ይህን ስሙ።
ዕን. 3፡14 የአለቆችን ራስ በገዛ በትራቸው ወጋህ እኔን ይበትኑ ዘንድ እንደ ዐውሎ ነፋስ መጡ ችግረኛውን በስውር ለመዋጥ ደስታቸው ነው።
ዘካ. 7፡10 መበለቲቱንና ድሀ አደጉን፥ መጻተኛውንና ችግረኛውን አትበድሉ ከእናንተም ማንም በወንድሙ ላይ ክፉውን ነገር በልቡ አያስብ።
ማቴ. 11፡5-6 ዕውሮች ያያሉ አንካሶችም ይሄዳሉ፥ ለምጻሞችም ይነጻሉ ደንቆሮችም ይሰማሉ፥ ሙታንም ይነሣሉ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው።
ማቴ. 19፡16-21 እነሆም፥ አንድ ሰው ቀርቦ። መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ? አለው።
እርሱም፦ ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ አለው። እርሱም፦ የትኞችን? አለው። ኢየሱስም፦ አትግደል፥ አታመንዝር፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው። ጐበዙም። ይህንማ ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ፥ ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው? አለው።ኢየሱስም፦ ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው።
ማቴ. 26፡7-11 አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው። ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው ተቈጡና። ይህ ጥፋት ለምንድር ነው? ይህ በብዙ ዋጋ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበርና አሉ። ኢየሱስም ይህን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ መልካም ሥራ ሠርታልኛለችና ሴቲቱንስ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ?
ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፥ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም፤
ማር. 12፡41-43 ኢየሱስም በመዝገብ አንጻር ተቀምጦ ሕዝቡ በመዝገብ ውስጥ ገንዘብ እንዴት እንዲጥሉ ያይ ነበር፤ ብዙ ባለ ጠጎችም ብዙ ይጥሉ ነበር፤ አንዲትም ድሀ መበለት መጥታ አንድ ሳንቲም የሚያህሉ ሁለት ናስ ጣለች። ደቀ መዛሙርቱንም ጠርቶ። እውነት እላችኋለሁ፥ በመዝገብ ውስጥ ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህች ድሀ መበለት አብልጣ ጣለች፤
ሉቃ. 14፡12-14 የጠራውንም ደግሞ እንዲህ አለው፦ ምሳ ወይም እራት ባደረግህ ጊዜ፥ እነርሱ ደግሞ በተራቸው ምናልባት እንዳይጠሩህ ብድራትም እንዳይመልሱልህ፥ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን ዘመዶችህንም ባለ ጠጎች ጎረቤቶችህንም አትጥራ።
ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፤ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና።
ሉቃ. 19፡8 ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን። ጌታ ሆይ፥ ካለኝ ሁሉ እኵሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደ ሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው።
ሮሜ. 15፡25-26 አሁን ግን ቅዱሳንን ለማገልገል ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ። መቄዶንያና አካይያ በኢየሩሳሌም ቅዱሳን መካከል ያሉትን ድሆች ይረዱ ዘንድ ወደዋልና።
ሮሜ. 13፡3 ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።
2ቆሮ. 6፡10 ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።
2ቆሮ. 8፡9 የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።
2ቆሮ፣ 9፡8-9 በተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።
ገላ. 2፡9-10 ደግሞ የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው፥ አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ኬፋ ዮሐንስም እኛ ወደ አሕዛብ እነርሱም ወደ ተገረዙት ይሄዱ ዘንድ ለእኔና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤ ድሆችን እናስብ ዘንድ ብቻ ለመኑን፥ ይህንም ደግሞ ላደርግ ተጋሁ።
ያዕ. 2፡1-6 ወንድሞቼ ሆይ፥ በክብር ጌታ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እምነት ለሰው ፊት በማድላት አትያዙ። የወርቅ ቀለበት ያደረገና የጌጥ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤአችሁ ቢገባ፥ እድፍ ልብስም የለበሰ ድሀ ሰው ደግሞ ቢገባ፥ የጌጥ ልብስም የለበሰውን ተመልክታችሁ። አንተስ በዚህ በመልካም ስፍራ ተቀመጥ ብትሉት፥ ድሀውንም። አንተስ ወደዚያ ቁም ወይም ከእግሬ መረገጫ በታች ተቀመጥ ብትሉት፥ ራሳችሁን መለያየታችሁ አይደለምን? ክፉ አሳብ ያላቸውም ዳኞች መሆናችሁ አይደለምን? የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድሆች አልመረጠምን? እናንተ ግን ድሆችን አዋረዳችሁ። ባለ ጠጎቹ የሚያስጨንቁአችሁ አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤትም የሚጎትቱአችሁ እነርሱ አይደሉምን?