Thursday, May 17, 2012

በኢትዮጵያ ያሉ ችግረኛ ሕጻናትን እንርዳ


እንዴት ናችሁ ወንድሞችና እህቶች፣  

ሌሎችን መርዳት እንዳለብን ስናስብ ብዙ ጊዜ፣ የራሳችን ጉድለቶች ወደ አይምሮአችን መምጣታቸው አይቀርም። ‘’ስንት ጉድለት እያለብኝ፣ እንዴት ነው ሌላውን መርዳት የምችለው?’’ እንል ይሆናል። እንደ እኔ እምነት ጥያቄው በራሱ ስህተት ባይኖረውም ‘በውስጡ የሸሸገው ስስት እና ራስ ወዳድነት ሊኖረው ይችል ይሆናል’ የሚል ፍርሃት ግን አለኝ።

መቼም ቢሆን ፍላጎቶቻችን አይሞሉም። አንዱ ሲሞላ ሌላ በር ይከፈታል፣ እሱም ሲሞላ ሌላ ይመጣል። በሰው ፍላጎት ውስጥ በቃኝ የሚል ምኞት ያልተፈጠረ እስኪመስል ድረስ፣ አንዱን ስናገኝ ሌላውን ለመሙላት መባዘናችን የተለመደ የቀን ተቀን ተግባራችን ነው ብል ያጋነንኩ አይመስለኝም።

ሁለት ያለው አንዱን ይስጥ የሚለው የጌታችን እና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ፣ የሚመለከተን እስካይመስል ድረስ ኑሮአችን ሁሉ በማግበስበስ እና በማከማቸት ላይ ያተኮረ ነው የሚለው ሃሳብ በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የምንኖር ክርስቲያኖችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከት ይመስለኛል።

ራሳችንን እና ዘመድ አዝማዶቻችንን ወይም ቤተሰቦቻችንን ብቻ ከማየት አዙሪት ወጥተን ብድራችንን የማይከፍሉትን፣ መልሰው ሊያመሰግኑን የማይችሉትን ሌሎች ችግረኞችን ለመርዳት በመነሳት ሙሉ ክብር ለእግዚአብሔር እናምጣ።

ትህትና ሊጎድለው ይችል ይሆናል ብዬ ላሰብኩት ጽሑፌ ይቅርታችሁን አየለመንኩ፣ ከዚህ ደብዳቤ ጋር አባሪ የሆነውን የፕሮጀክት ሃሳብና የቪዲዮ ሰነድ በመመልከት ያላችሁን አስተያየት እንድትለግሱኝ እጠይቃለሁ።

እግዚአብሔር ለስሙ የምናሳየውን በጎነት ይረሳ ዘንድ ሰው አይደለም።

____________________________________________________________________________________________________________

የፕሮጀክቱ ስያሜ፡ ቅድሚያ ለሕጻናት Kids First 

የፕሮጀክቱ ባለቤት፡ ሕጻናቱን ስፖንሰር የሚያደርጉ አባላት ሁሉ

ፕሮጀክቱ ስራ የሚጀምርበት ጊዜ፡ እ.ኤ.አ. ጥር 2012 ዓ.ም.

የፕሮጀክቱ ቆይታ፡ ቆይታው ለአንድ አመት ይሆንና በየአመቱ መጨረሻ በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ከጳጉሜ 1-5 የሚታደስ ይሆናል። ስፖንሰሮች ለአንድ አመት ሕጻኑን ለማገዝ ቃል ከገቡ ቃላቸውን የመጠበቅ የሕሊና ግዴታ ይኖርባቸዋል። በአመቱ መጨረሻ ግን ስፖንሰርሺፑን የማደስ ወይም ያለማደስ ውሳኔ ሙሉ በሙሉ የራሳቸው ይሆናል።

እገዛው የሚዳስሳቸው ዘርፎች፡ 1. ትምህርት 2. ጤና እና 3. መንፈሳዊ

ትምህርት
‘መሃይምነት፣ ከችግር እና ረሃብ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እናደለው’ እ.ኤ.አ. 2005 ዓ.ም. የወጣው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትሪፖርት ያስረዳል።

ምንም እንኳን ትምህርት በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎች ነጻ ቢሆንም፣ ከትምህርት ጋር ተያያዥ የሆኑ ወጪዎች ማለትም የዩኒፎርም ወጪ፣ የደብተር፣ የእርሳስ፣ የእስክሪቢቶ፣ እና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች ብዙ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ሊሸፍኑት ከሚችሉት በላይ እጅግ ከባድ ነው። በዚህም ምክንያት በርካታ ሕጻናት በትምሕርታቸው ላይ ከማተኮር ይልቅ ይህንን ወጪ ለመሸፈን ያለእድሚያቸው ስራ ለመስራት ይገደዳሉ። በሂደትም በቀላል የማይቆጠሩቱ ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ። በኢትዮጵያ ከ50% ያነሰ ቁጥር ያላቸው ልጃገረዶች ብቻ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ መሆናቸው ለዚህ ሁነኛ አብነት ነው።

ይህንን ችግር ለመቅረፍ፣ ይህ ፕሮጀክት ከትምህርት ጋር ተያያዥ የሆኑ ወጪዎችን በመሸፈን ሕጻናት ከትምህርት ገበታቸው ላይ እንዳይፈናቀሉ ይረዳል።    

የትምሕርት ግብአቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያጠቃልላል፦
በአመት አንድ ጊዜ የሚታደል ዩኒፎርም

በአመት ሁለት ጊዜ የሚታደል የመማሪያ ደብተር

በአመት አንድ ጊዜ የሚታደል የመማሪያ መጽሐፍ

በአመት ሁለት ጊዜ የሚታደል እስክሪቢቶ እና እርሳስ

ሌሎች ተዛማጅ ግብአቶች

ጤና
ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቀላሉ መከላከል በሚቻል የማላሪያ በሽታ እንደሚሞቱ የምናውቅ ስንቶች ነን? ቁጥሩ ዘግናኝ ሊሆን ይችላል። ሃቁ ግን ይኸው ነው። ለአብነት ይህን ጠቀስን እንጂ በተመጣጠነ ምግብ እጦት ምክንያት በቀላሉ መከላከል በሚቻል በሽታዎች የሞመቱትን ሕጻናት ቤት ይቁጠራቸው። የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት የሚለው ሃሳብ ለብዙ ኢትዮጵያውያን ሕጻናት እንደ ሰማይ የራቀ ሃቅ ነው ብንልና ጥያቄውን ‘ምን ያህል ሕጻናት በቀን ሶስት ጊዜ በልተው ያድራሉ?’ በሚል እናሻሽለው ብንል እንኳን፣ ቁጥሩ አሁንም ዘግናኝ ነው።

እናም የተወሰኑ የምግብ አይነቶች በየወሩ ለእነዚህ ሕጻናት ማድረስ ቢቻል፣ ጤናቸውን ከመጠበቅ ባሻገር ትምሕርታቸውን ለመከታተል የተመቻቸ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል።

የጤና ግብአቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያጠቃልላል፦
በየወር የሚታደል የምግብ ዘይት
በየወር የሚታደል የልብስ ሳሙና
በየወር የሚታደል የስንዴ ዱቄት
በየወር የሚታደል ሳሙና
በአመት አንድ ጊዜ የሚታደል አንድ ሱሪ
በአመት አንድ ጊዜ የሚታደል አንድ ጥንድ ጫማ
በአመት አንድ ጊዜ የሚታደል ሁለት ጥንድ ካልሲና የውስጥ ሱሪ
በአመት አንድ ጊዜ የሚበጀት የጤና ጣቢያ ወጪ

መንፈሳዊ
ይህ ሕብረት ከእርዳታ ማስተባበሪያ ድርጅት ስራ ያለፈ ግብ ሊኖረው ይገባል። እውነተኛ እና ዘላቂ የሰው ልጅ ለውጥ ከመንፈሳዊ ለውጥ ጋር በተያያዘ መንገድ ብቻ እውን ሊሆን እንደሚችል ጠንካራ እምነታችን ነው። ያለ ምንም ሃይማኖታዊ መስፈርት ፍቅራችንን ለማንኛውም ሕጻን ለመግለጽ የምንተጋ ቢሆንም፣ የፍቅራችን ምንጩ ይህንን እውነት ኖሮ ያሳየን ጌታችን እና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ግን ከመናገር ወደ ኋላ የምንል አይሆንም ። ሕጻናት እግዚአብሔርን በመፍራት እና በመውደድ እንዲያድጉ በምንገልጽላቸው ፍቅር ለማስረዳት እንጥራለን።

የመንፈሳዊ ግብአቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያጠቃልላል፦
በአመት ሁለት ጊዜ የሚታደል መንፈሳዊ መጻሕፍት
በአመት ሁለት ጊዜ የሚታደል የመማሪያ ደብተር
በአመት አንድ ጊዜ የሚታደል መጽሐፍ ቅዱስ
በሳምንት አንድ ቀን የሚሰጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት

ሕጻናቱን ስፖንሰር የሚያደርጉ ሰዎችን ለማግኘት ስራ ላይ የሚውለው የትኩረት ቅደም ተከተል ስትራቴጂ፡
1.   በዚህ ፕሮጀክት በቀዳሚ ትኩረት  የሚደረግባቸው ስፖንሰሮች፣ በውጪ አገር የሚገኙ የተሃድሶ ቤተ ክርስቲያን አባላት እና የቀድሞ አባላት ይሆናሉ። 


2.     በሁለተኛ ደረጃ ስፖንሰር እንደሚሆኑ የሚጠበቁት ደግሞ በውጭ አገር የሚኖሩ እና ስለ ተሃድሶ ቤተ ክርስቲያን በቂ እውቀት ያላቸው፣ በዚህም ምክንያት በፕሮጀክቱ ላይ በቀላሉ እምነታቸውን ሊጥሉ የሚችሉ ይሆናሉ። 


3.   በሶስተኛ ደረጃ ትኩረት የሚደረግባቸው ስፖንሰሮች ደግሞ፣ በቁጥር አንድ እና ሁለት ላይ የተጠቀሱት ሰዎች በቅርበት የሚያውቋቸው ቤተሰቦች፣ ዘመዶች እና ጓደኞች ይሆናሉ። 

4.      በመጨረሻም፣ በአገር ውስጥ የሚኖሩ እና ሕጻናቱን ስፖንሰር ለማድረግ የሚሹ አባላትን ለመመልመል ጥረት ይደረጋል።

የስፖንሰርሺፑ አይነት፡ ሙሉ ወይም ግማሽ ስፖንሰርሺፕ


ለአንድ ሕጻን ሙሉ ስፖንሰር ለመሆን የሚያስፈልገው ወራዊ ወዋጮ፡ $25 ዶላር ይሆናል። ሆኖም ግን ስፖንሰር አድራጊው እንደ አቅሙና ፍላጎቱ ከአንድ በላይ ልጆችን ስፖንሰር ማድረግ ይችላል።


በግማሽ ስፖንሰርሺፕ ሳይን አፕ ለማድረግ በየወሩ $12.50 ዶላር መዋጮ ማድረግ ያስፈልጋል። ይህንን መዋጮ በቀጣዩ የእድሳት አመት በማሳደግ ለአንድ ልጅ ወይም ከዛ በላይ ለሆኑ ልጆች ሙሉ ስፖንሰር መሆን ይቻላል።

የገንዘቡ አላላክ ሁኔታ፡ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ ስፖንሰሮች ሙሉ ስማቸውን እና ስፖንሰር የሚያደርጉትን ሕጻን ስም ጠቅሰው አዲስ አበባ ለሚገኘው የፕሮጀክት አስተባባሪ በየወሩ ይልካሉ። አልያም በአሜሪካ በሚገኘው የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አካውንት ገቢ በማድረግ አስተባባሪው ወደ አገር ቤት እንዲልክ ማድረግ ይቻላል። ይህን በማድረግ የመላኪያ ወጪዎን መቀነስ ይችላሉ።

ፕሮጀክቱ እያደገ ሲመጣ የራሱ ሒሳብ ቁጥር ስለሚኖረው ገንዘቡን በሒሳብ ቁጥሩ መላክ ይቻላል።


በአዲስ አበባ ያለው የፕሮጀክቱ አስተባባሪ
ሙሉ ስም፡ ሳሙኤል ሙሉጌታ (Samuel Mulugeta)
ሃላፊነት፡ የተሃድሶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ክፍል መሪ እና Kids First -  ቅድሚያ ለሕጻናት ፕሮጀክት አስተባባሪ
ስልክ ቁጥር፡ 011 251 911 483679
ኢ-ሜይል፡ samimulu@gmail.com


በአሜሪካ ያለው የፕሮጀክቱ አስተባባሪ
ሙሉ ስም፡ አዳነው ዲሮ ዳባ (Adanew Diro Daba)
ሃላፊነት፡ የ Kids First -  ቅድሚያ ለሕጻናት ፕሮጀክት አስተባባሪ
የባንክ አካውንት ቁጥር፡
Naomi Worknesh Getaneh
Bank of America
Account # 4570 0719 5163
Tucson, Arizona
ስልክ ቁጥር፡ 520 256 9475
ኢ-ሜይል፡ kidsfirstethiopia@gmail.com

ገንዘቡ ለተባለለት አላማ መዋሉን በምን አረጋግጣለሁ? ማንኛውም ስራ ከአደጋ (ሪስክ) ሙሉ በሙሉ የፀዳ ሊሆን አይችልም። ይህንን ማድረግ እንችላለን የሚል ቃል ለመግባትም አንችልም። ሆኖም ግን የሚከተሉትን የመከታተያ መንገዶች በመጠቀም ገንዘቡ በተቻለ መጠን ለተገቢው አላማ እንዲውል ያልተቆጠበ ጥረት እናደርጋለን፦
1.   ስፖንሰሮቾ ገንዘቡን ከላኩ በኋላ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ፣ ገንዘቡ መድረሱን እና ለታቀደለት አላማ መዋሉን ለስፖንሰር አድራጊዎቹ ቢያንስ በየሁለት ወሩ ተጨባጭ ሪፖርት በማቅረብ የማረጋገጥ ሃላፊነት ይኖርበታል። ይህ ማረጋገጫ የተረጂው ልጅ ፊርማ፣ የአሳዳጊው ፊርማ፣ የእቃ ግዢ ፈጻሚው አካል ፊርማ እና የቤተ ክርስቲያኒቱ መጋቢ ፊርማ የያዘ ማስረጃ ማቅረብን የሚያጠቃልል ይሆናል።
2.     ስፖንሰሮቹ፣ ቢያን በየወሩ ስፖንሰር ለሚያደርጉት ልጅ ወይም አሳዳጊ በመደወል ስለሁኔታው በቀጥታ ለመረዳት ጥረት ቢያደርጉ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ከመረዳት አልፎ ሁኔታውን በመጠቀም በሚረዱት ሕጻን ውስጥ ሌሎች ጠቃሚ ተጽእኖዎችን ለመፍጠር ያስችላቸዋል።
3.     ስፖንሰሩ በተለያየ አጋጣሚ ወደ አገር ቤት የመሄድ አጋጣሚ በሚያገኝበት ጊዜ ራሱ በአካል ለማረጋገጥ ጥረት ማድረግ ወይም በአገር ቤት የሚገኙ ዘመዶቹ ወይም ወዳጆቹ እደላው በሚካሄድበት እለት ወይም በማንኛው የስራ ሰአት በቤተ ክርስቲያኒቱ በመገኘት ሁኔታውን እንዲያጣሩ ሊያደርግ ይችላል።      

የወጪ ዝርዝር (2012 ዓ.ም.)

  1. ትምሕርት
ተ.ቁ.
ዝርዝር
ወራዊ ወጪ
አመታዊ ወጪ
መግለጫ
1
በአመት አንድ ጊዜ የሚታደል ዩኒፎርም
200 ብር
200 ብር

2
በአመት ሁለት ጊዜ የሚታደል የመማሪያ ደብተር
-
200 ብር
በአመት 20 ደብተር ቢያስፈልግና የእያንዳንዱ ዋጋ 10ብር ቢሆን
3
በአመት አንድ ጊዜ የሚታደል የመማሪያ መጽሐፍ

100 ብር
10 የመማሪያ መጽሐፎች እያንዳንዳቸው 10 ብር ቢሆን
4
በአመት ሁለት ጊዜ የሚታደል እስክሪቢቶ እና እርሳስ
5ብር
50 ብር
ለ10 የትምሕርት ወራት
5
ሌሎች ተዛማጅ ግብአቶች

100ብር
ፎቶ፣መታወቂያ፣ ኮፒ፣መዋጮ፣እና ሌሎች

አጠቃላይ
650ብር


  1. ጤና
ተ.ቁ.
ዝርዝር
ወራዊ ወጪ
አመታዊ ወጪ
መግለጫ
1
በወር የሚታደል የምግብ ዘይት
60 ብር
720 ብር
60 ሲባዛ በ12
2
በወር የሚታደል የስንዴ ዱቄት
50 ብር
600 ብር
50 ሲባዛ በ12
3
በወር የሚታደል የልብስ ሳሙና
20 ብር
240 ብር
20 ሲባዛ በ12
3
በአመት አንድ ጊዜ የሚታደል አንድ ሱሪ
-
70 ብር

4
በአመት አንድ ጊዜ የሚታደል አንድ ጥንድ ጫማ
-
150 ብር

5
በአመት አንድ ጊዜ የሚታደል ሁለት ጥንድ ካልሲና የውስጥ ሱሪ
-
100ብር

6
በአመት አንድ ጊዜ የሚበጀት የጤና ጣቢያ ወጪ
-
500 ብር


አጠቃላይ
2380ብር


  1. መንፈሳዊ
ተ.ቁ.
ዝርዝር
ወራዊ ወጪ
አመታዊ ወጪ
መግለጫ
1
በአመት ሁለት ጊዜ የሚታደል መንፈሳዊ መጻሕፍት
-
50 ብር

2
በአመት ሁለት ጊዜ የሚታደል የመማሪያ ደብተር
-
40 ብር
በአመት 4 ደብተር ቢያስፈልግና የእያንዳንዱ ዋጋ 10ብር ቢሆን
3
በአመት አንድ ጊዜ የሚታደል መጽሐፍ ቅዱስ

60 ብር
ቢሆን
4
በሳምንት አንድ ቀን የሚሰጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት
20
240 ብር
የትራንስፖርት ወጪ በሳምንት 5 ብር

አጠቃላይ
390ብር


  1. ስራ ማስኬጃ
ተ.ቁ.
ዝርዝር
ወራዊ ወጪ
አመታዊ ወጪ
መግለጫ
1
የታክሲ
20ብር
240
20 ሲባዛ 12
2
የተሸካሚ
20ብር
240
20 ሲባዛ 12
3
የስልክ
15 ብር
180
15 ሲባዛ 12

አጠቃላይ
660ብር


  1. አጠቃላይ አመታዊ ወጪ
ተ.ቁ.
ዝርዝር
አመታዊ ወጪ
መግለጫ
1
ትምሕርት
650ብር

2
ጤና
2380ብር

3
መንፈሳዊ
390ብር

4
ስራ ማስኬጃ
660ብር


አጠቃላይ አመታዊ ወጪ በብር
4080ብር


አጠቃላይ ወራዊ ወጪ በብር
340 ብር
4080 ብርን ለ12 ማካፈል

አጠቃላይ አመታዊ ወጪ በብር
240 ዶላር
4080 ብርን ለ17 ማካፈል

አጠቃላይ ወራዊ ወጪ በብር
20 ዶላር
240 ዶላርን ለ12 ማካፈል


25 ዶላር
5 ዶላር ኮንቲንጀንሲ

ማሳሰቢያ፡ ወጪው በፍጥነት ተለዋዋጭ የሆነውን የአገር ቤት ገበያ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በወር የ $5 ዶላር ኮንቲንጀንሲ እንዲያካትት ተደርጓል። 

አስተያየቶን በመስጠት እና የድርሻዎን በመወጣት ፕሮጀክቱ የብዙ ሕጻናትን ሕይወት እንዲለውጥ ምክንያት ይሁኑ።

በፕሮጀክቱ ታቅፈው ችግረኛ ሕጻናትን ስፖንሰር ለማድረግ የሚሹ ከሆነ፣ በሚከተሉት አድራሻዎች ያግኙን፣ kidsfirstethiopia@gmail.com ወይም samimulu@gmail.com ወይም የሚከተሉትን ስልክ ቁጥሮች በመጠቀም ይደውሉልን። 520 256 9475 (USA, Adanew Diro) Or 011 251 911483679 (Ethiopia, Samuel Mulugeta)::

መጽሐፈ ምሳሌ 19፡17 ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።

አዳነው ዲሮ
በአሜሪካ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ